የባለአክሲዮኖች 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ
በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አንቀጽ 366(1)፣ 367(1)፣ 370 እና 371 እንዲሁም በአ/ማኅበሩ የመመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 18 መሰረትየባለአክሲዮኖች 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እሑድ ህዳር 06 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ራስ ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ስለሚካሂድ የተከበራችሁ የማኅበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀን፣ሰዓትና ቦታ በጉባኤዎቹላይ እንድትገኙ የማኅበሩ ዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል።
1. ማኅበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
• የማኅበሩ ስም፦ አቦል ቡና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ፣
• የማኅበሩ አይነት፦ በአነስተኛ የፋይናንስ ስራ ላይ የተሰማራ የአክሲዮን ማኅበር፣
• የማኅበሩ ዋና መስሪያ ቤት፦ አዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 9፣ የቤት ቁጥር 620፣
• የማኅበሩ የተፈረመ ካፒታል፡-ብር 98,100,000.00፣
• የማኅበሩ የተከፈለ ካፒታል፦ ብር 50,800,000.00፣
• የማኅበሩ የንግድ የምዝገባ ቁጥር፦ MT/AA/3/0057177/2016፣
• የማኅበሩ ፋይናንስ ስራ ፈቃድ ቁጥር፦MFI/066/2024፣
• የማኅበሩ ድረ-ገጽ፡- www.abollbunnamfi.com፣
2. የ4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች፤
2.1 የጉባዔውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፤
2.2 አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበልና የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማጽደቅ፤
2.3 የ2025/2026 የሂሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ መወሰን፤
2.4 የ2025/2026 የሂሳብ ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ መወሰን፤
2.5 ከ2019 እስከ 2021 ላሉት ተከታታይ ሦስት ዓመታት የሚያገለግሉ የውጭ ኦዲተር መሾም እና ክፍያቸውን መወሰን፤
2.6 የ2025/2026 የሂሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈል ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
2.7 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የ2025/2026 የሂሳብ ዓመት ዓመታዊ የሥራ ዋጋ እና የ2026/2027 የሂሳብ ዓመት ወርሃዊ አበልክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
2.8 ለቀጣይ ሦስት ዓመታት የሚያገለግሉ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ምርጫ ማከናወን፤
2.9 የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ፤
3. ማሳሰቢያ፣
3.1 በጉባኤው መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 03 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ በአዲስአበባ ከተማ፣ ደንበል ሲቲ ሴንተር ጀርባ በሚገኘው ኮሜርሻል ኖሚኒስ ህንጻ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤትበመቅረብ የውክልና ቅጽ በመሙላት ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ የተረጋገጠ የውክልና ሥልጣን ማስረጃ ዋናውን እና ፎቶኮፒ ይዘው በመቅረብ በጉባኤው ላይ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን ቦርዱ ያሳውቃል፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማኅበሩ ጠቅላላጉባኤ በማናቸውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
3.2 የአክሲዮን ማኅበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አዋጅላይ በተደነገገው መሰረት ተገቢውን መረጃ ለማሟላት እንዲረዳ የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ካርድ (ፋይዳ) ዋናውንና ኮፒውንበመያዝ እንዲሁም የውጭ ዜግነት ያላችሁ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናችሁንየሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ይዛችሁ መቅረብ ያለባችሁ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን።
የአቦል ቡና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ
