ለተከበራችሁ የአቦል ቡና ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ
አቦል ቡና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በንግድ ሕግ አንቀጽ 366(1)፣ 367(1)፣ 370)፣ 371፣ እና 400 እንዲሁም በአ/ማኅበሩ የመመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 18 መሰረት የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ እና 1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ታህሳስ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ራስ ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ጀምሮ ጉባኤውን ያካሂዳል፡፡በመሆኑም የተከበራችሁ የአክሲዮን ማኅበሩ ባለአክስዮኖች በተጠቀሰው ቀን፣ ሠዓትና ቦታ እንድትገኙልን የማኅበሩ ዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
1. ማኅበሩ የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
- የማኅበሩ ስም፡- አቦል ቡና ማይክሮ ፋይናንስ አ/ማኅበር፣
- የማኅበሩ አይነት፡- አነስተኛ የፋይናንስ ሥራ ላይ የተሰማራ የአክስዮን ማህበር
- የማኅበሩ የተፈረመ ካፒታል፡- ብር 98,100,000.00
- የማኅበሩ የተከፈለ ካፒታል፡- ብር 40,115,000.00
- የንግድ የምዝገባ ቁጥር፡-MT/AA/3/0057177/2016፣
- የፋይናንስ ሥራ ፍቃድ ቁጥር፡-MFI/066/2024፣
- የማኅበሩ ዋና መስሪያ ቤት፡- አድራሻ አ/አበባ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 9 የቤት ቁጥር 620፣
- የ3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች፣
- አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበልና የተደረጉ አክሲዮን ዝዉዉሮችን ማሳወቅ፣
- እ.ኤ.አ የ2024/2025 የሂሳብ አመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ መወሰን፤
- እ.ኤ.አ የ2024/2025 የሂሳብ አመት የዉጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ መወሰን፤
- እ.ኤ.አ በ2024/2025 የሂሳብ አመት የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈል ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
- የ2024/2025 ሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ የሥራ ዋጋ እና እ.ኤ.አ የ2025/2026 ሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርኃዊ አበል መወሰን፣
- የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ፣
- የ1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
- የማይክሮ ፋይናንሱን የመመስረቻ ጽሑፍ ማሻሻል፣
- የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ፣
- ማሳሰቢያ፦
- በጉባኤ ላይ በአካል መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ ደንበል ሲቲ ሴንተር ጀርባ ኮሜርሻል ኖሚኒስ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ከሚገኘው የተቋሙ ዋና መሥሪያ ቤት በመቅረብ የውክልና ቅጽ በመሙላት ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ የተረጋገጠ የውክልና ሥልጣን ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ በጉባኤው ላይ እንዲሳተፉ ከወዲሁ እናሳውቃለን፤
- የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በጉባኤዉ ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አዋጅ ላይ በተደነገገዉ መሰረት ተገቢዉን መረጃ ለማሟላት እንዲረዳ የኢትዮጵያ ዲጅታል መታወቂያ ካርድ (ፋይዳ) ዋናዉንና ኮፒዉን በመያዝ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳዉቃለን።
የአቦል ቡና ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ዳይሬክተሮች ቦርድ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-251-11 558-22-58 ወይም 0905-111105 ወይም 0905-111104
